ወደ ዋናው ይዘት ይዝለሉ

ያመ - ያልተማከለ መተገበሪያዎች

በኢተርየም አቅም የተገነቡ መሣሪያዎች እና አገልግሎቶች

Dappዎች ኢቴርያምን በመጠቀም አሁን ላይ ያሉትን የንግድ ሞዴሎችን በመቀልበስ ወይም አዳዲሶችን በመፈልሰፍ እያደጉ ያሉ የመተግበሪያዎች እንቅስቃሴ ናቸው።

ኮምፕዩተር የሚጠቀም doge የሚያሳይ ምስል

ጀምር

Dappን ለመሞከር ቦርሳ እና የተወሰነ ETH ያስፈልግዎታል። ቦርሳው እንዲገናኙ ወይም እንዲገቡ ያስችልዎታል። ETH ደግሞ ማንኛውንም የግብይት ክፍያ ለመክፈል ያስፈልግዎታል።

1. አንዳንድ ETH ያግኙ

የDapp ድርጊቶች የግብይት ክፍያ ያስከፍላሉ

2. ቦርሳ ያዘጋጁ

ቦርሳዎ የእርስዎ ወደ dapp "መግቢያ" ነው።

3. ዝግጁ ናችሁ?

ለመሞከር የሚፈልጉትን dapp ይምረጡ

Beginner friendly

A few dapps that are good for beginners. Explore more dapps below.

የUniswap አርማ

Uniswap

ቶከኖችዎን በቀላሉ ይቀይሩ። በማህበረሰቡ ተወዳጅነትን ያተረፈ እና አውታረ መረቡ ውስጥ ካሉ ሰዎች ጋር ቶከኖችን ለመገበያየት የሚያስችል።

finance
ክፈት Uniswap(opens in a new tab)
የOpenSea አርማ

OpenSea

ውስን ስሪት ያላቸውን እቃዎችን ይግዙ፣ ይሽጡ፣ ይወቁ እና ይገበያዩ።

collectibles
ክፈት OpenSea(opens in a new tab)
የGods Unchained አርማ

Gods Unchained

ስትራቴጂካዊ የግብይት ካርድ ጨዋታ። በገሃዱ አለም ላይ መሸጥ የሚችሉትን ካርዶችን እየተጫወቱ ያግኙ።

gaming
ክፈት Gods Unchained(opens in a new tab)
የEthereum Name Service አርማ

Ethereum Name Service

ለኢቴርየም አድራሻዎች እና ላልተማከሉ ድረገጾች ለተጠቃሚ ምቹ የሆኑ ስሞች።

social
ክፈት Ethereum Name Service(opens in a new tab)

dappዎችን ይመልከቱ

ብዙ dappዎች አሁንም በሙከራ ላይ ሲሆኑ ባልተማከሉ አውታረ መረቦች የተለያዪ መንገዱችን በመሞከር ላይ ናቸው። ነገር ግን በቴክኖሎጂ፣ በፋይናንሺያል፣ በጨዋታ እና በስብስብ ምድቦች ውስጥ አንዳንድ የተሳካላቸው ቀደም በለው የተንቀሳቀሱም ነበሩ።

ምድብ ይምረጡ

ያልተማከለ ፋይናንስ

እነዚህ ክሪፕቶከረንሲዎችን በመጠቀም የፋይናንስ አገልግሎቶችን መገንባት ላይ የሚያተኩሩ መተግበሪያዎች ናቸው። እንደ ማበደር፣ መበደር፣ ወለድ ማግኘት እና የግል ክፍያዎችን መፈጸምን የመሳሰሉ አገልግሎቶችን ይሰጣሉ - ምንም የግል መረጃ አያስፈልግም።

ሁልጊዜ የራስዎን ጥናት ያድርጉ

ኢቴሬየም አዲስ ቴክኖሎጂ ስለሆነ አብዛኛዎቹ ጥቅሞቹ አዲስ ናቸው። ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ ከማስቀመጥዎ በፊት፣ አደጋዎቹን መረዳትዎን ያረጋግጡ።

ማበደር እና መበደር

ቶከን መለወጫዎች

Demand aggregators

Bridges

ኢንቨስትመንቶች

ፖርትፎሊዮዎች

የመድህን ዋስትና

ክፍያዎች

ገንዘብ ማሰባሰብያ

Derivatives

Liquid staking

የንግድ እና የትንበያ ገበያዎች

Want to browse more apps?

Check out hundreds of dapps(opens in a new tab)

ድንቁ አስማት ከጀርባ ያልተማከለ ፋይናንስ

ምንድነው ስለ ኢተርየም ያልተማከለ ፋይናንስ መተግበሪያዎችን እንዲዳብር የሚያስችለው?

ለመድረስ ክፍት

በኢቴርየም ላይ የሚሰሩ የፋይናንስ አገልግሎቶች የምዝገባ መስፈርቶች የላቸውም። ገንዘብና እና የበይነመረብ ግንኙነት ካሎት፣ ለመጀመር ዝግጁ ነዎት።

አዲስ የቶከን ኢኮኖሚ

ከነዚህ የፋይናንሺያል ምርቶች ላይ መስተጋብር የሚፈጥሩበት የቶከኖች ሌላ አዲስ አለም አለ። ሰዎች በኢተርየም ላይ ሁል ጊዜ አዳዲስ ቶከኖችችን እየገነቡ ነው።

ስቴብልኮይኖች

ቡድኖች ስቴብልኮይንን ገንብተዋል - አነስተኛ ተለዋዋጭነት ያለው ክሪፕቶከረንሲ። እነዚህን ያለ አደጋ ስጋት እና ጥርጣሬ ሙከራ እንዲያደርጉ ያስችሉዎታል።

እርስ በርስ የተያያዙ የፋይናንስ አገልግሎቶች

በኢቲሪየም ውስጥ ያሉ የፋይናንስ ምርቶች ሁሉም ሞጁላር እና እርስ በርስ የሚጣጣሙ ናቸው። የእነዚህ ሞጁሎች አዲስ አወቃቀሮች ሁል ጊዜ ገበያ ውስጥ እየመጡ ነው፣ እርስዎ በክርፕቶ ምን ማድረግ እንደሚችሉ እድል እየጨመሩ ነው።

ስላልተማከለ ፋይናንስ ተጨማሪ መረጃ
የአስማተኞች ምስል

ከDappዎች በስተጀርባ ያለው አስማት

Dappዎች እንደ መደበኛ መተግበሪያዎች ሊመስሉ ይችላል። ነገር ግን ከትዕይንቱ በስተጀርባ አንዳንድ ልዩ ባህሪያት አሏቸው፤ ምክንያቱም ሁሉንም የኢተርየም ልዕለ ኃያላንን ይወርሳሉ። Dappዎችን ከመደበኛ መተግበሪያዎች የሚለያቸው እነዚህ ናቸው።

ኢቴሬምን ታላቅ የሚያደርገው ምንድን ነው?

ባለቤት የለሽ

አንዴ ኢተርየም ላይ ከተሰማራ፣ የdapp ኮድ ሊወርድ አይችልም። እና ማንም ሰው የdappን ባህሪያት መጠቀም ይችላል። dappን የሰራው ቡድን ቢበታተንም እንኳን ሊጠቀሙበት ይችላሉ። አንዴ ኢቴሬየም ላይ ከሆነ እስከመቼም ድረስ እዚያው ይቆያል።

ከሳንሱር ነፃ

አብሮገነብ ያለው ክፍያዎች

ይሰኩ እና ይጫወቱ

ማንነትዎን የማይገልጽ መግቢያ

በክሪፕቶግራፊ የተደገፈ

መቆራረጥ የለም።

Dappዎች እንዴት እንደሚሰሩ

Dappዎች ባክኤንደ ኮዳቸው (ዘመናዊ ውሎች) በያልተማከለ አውታረ መረብ ላይ እንጂ የተማከለ ሰርቨር ላይ አይደለም። እነሱም ኢቲሪየምን ለመረጃ ማከማቻ እና ዘመናዊ ውሎች ለመተግበሪያ ሎጂክ ይጠቀሙታል።

ዘመናዊ ውል በሰንሰለት ላይ የሚኖሩ ህጎች ስብስብ ነው እናም ሁሉም እነዚህ ህጎች ያያል በእነዚህ ህጎች መሠረት በትክክል ይሄዳል። አንድ የሽያጭ ማሽን ያስቡ፡ በበቂ ገንዘብ እና ትክክለኛው ምርጫ ካቀረቡለት የሚፈልጉትን ዕቃ ያገኛሉ። እና እንደ መሸጫ ማሽኖች፣ ዘመናዊ ውሎች ልክ እንደ የእርስዎ ኢቲሪየም ሂሳብዎ ገንዘቦችን ሊይዙ ይችላሉ። ይህ ኮድ ስምምነቶችን እና ግብይቶችን ለማከናወን ያስችላል።

Dappዎች አንዴ በኢተርየም አውታረመረብ ላይ ከተሰማሩ በኋላ እነሱን መቀየር አይችሉም። Dappዎች ያልተማከሉ ይሆናሉ ምክንያቱም ቁጥጥር የሚደረግባቸው በውሉ ላይ በተፃፈው ሎጂክ እንጂ በግለሰብ ወይም በኩባንያ አይደሉም።

ይህ ገፅ አግዞዎት ነበር?