ወደ ዋናው ይዘት ይዝለሉ

Ether (ETH) ምንድን ነው?

ለዲጅታል ወደፊታችን መገበያያ ገንዘብ

ETH ዲጂታል፣ ዓለም አቀፍ ገንዘብ ነው።

የኤቴርየም መተግበሪያዎች መገበያያ ገንዘብ ነው።

የአሁኑ ጊዜ የETH ዋጋ (በአሜሪካ ዶላር)

በመጫን ላይ ነው...
(የመጨረሻ 24 ሰዓታት)
ኤቴሪየም(ETH) ያግኙ
ስዎች በጋራ ሁነው Ether (ETHን) በአድናቆት ሲመለከቱ የሚያሳይ ምስል

ETH ክሪፕቶከረንሲ ነው። በበይነመረብ ላይ ሊጠቀሙበት የሚችሉት በጣም በአነስተኛ መጠን የሚገኝ ዲጂታል ገንዘብ ነው – ልክ እንደ ቢትኮይን። ለክሪፕቶ አዲስ ከሆኑ፣ ETH ከተለመደው ገንዘብ እንዴት እንደሚለይ እነሆ።

በእውነት የእርስዎ ነው።

ETH የራስዎ ባንክ እንዲሆኑ ያስችልዎታል። የእራስዎን ገንዘቦች እንደ ባለቤትነት ማረጋገጫ በቦርሳዎ መቆጣጠር ይችላሉ – ምንም አይነት ሶስተኛ ወገኖች አያስፈልጉም፡፡

በክሪፕቶግራፊ ደህንነቱ የተጠበቀ

የኢንተርኒት ገንዘብ አዲስ ሊሆን ይችላል ነገር ግን በአስተማማኝ ክሪፕቶግራፊ ደህንነቱ የተጠበቀ ነው። ይህ ቦርሳዎን፣ የእርስዎን ETH እና ግብይቶችዎን ይጠብቃል።

የአቻ ለአቻ ክፍያዎች

እንደ ባንክ ያሉ የመካከለኛ አገልግሎት ሳየጠቀሙ የእርስዎን ETH መላክ ይችላሉ። ልክ ገንዘብን በአካል እንደመስጠት ነው፣ ነገር ግን ደህንነቱ በተጠበቀ ሁኔታ ከማንም ጋር፣ በማንኛውም ቦታ፣ በማንኛውም ጊዜ ማድረግ ይችላሉ።

ማእከላዊ ቁጥጥር የለም

ETH ያልተማከለ እና ዓለም አቀፋዊ ነው ። ተጨማሪ ETH ለማተም የሚወስን ወይም የአጠቃቀም ውሉን የሚቀይር ኩባንያ ወይም ባንክ የለም።

ለማንም ሰው ክፍት

ETHን ለመቀበል የኢንተርኔት ግንኙነት እና ቦርሳ ብቻ በቂ ነው። ክፍያዎችን ለመቀበል የባንክ ሒሳብን ማግኘት አያስፈልገዎትም።

በተለያዩ መጠኖች የቀረበ

ETH እስከ 18 አስርዮሽ ቤት ድረስ ይከፈላል ስለዚህ 1 ሙሉ ETH መግዛት አያስፈልግዎትም። ከፈለጉ በአንድ ጊዜ ክፍልፋዮችን መግዛት ይችላሉ – እስከ 0.0000000000000001 ETH ድረስ።

አንዳንድ ኢቴርየም መግዛት ይፈልጋሉ? ኢቲሪየምን እና ETHን መቀላቀል የተለመደ ነገር ነው። ኢቲሪየም ብሎክቼን ሲሆን ETH ደግሞ የኢቲሪየም ዋና ንብረት ነው። ምናልባትም መግዛት የሚፈልጉት ETHን ነው። ስለ ኢቲርየም ተጨማሪ መረጃ

ስለ ETH ልዩ የሆነው ነገር ምንድን ነው?

በኢቲሪየም ላይ ብዙ ክሪፕቶከረንሲዎችና ብዙ ሌሎች ቶከኖች አሉ፣ ግን ETH ብቻ ሊያደርጋቸው የሚችላቸው አንዳንድ ነገሮች አሉ።

ETH ኢቲሪየምን እንደ ነዳጅ ያንቀሳቅሳል ደህንነቱንም ይጠብቃል።

ETH የኢቲሪየም የሕይወት ደም ነው። ETHን ሲልኩ ወይም የኢቲሪየም መተግበሪያን ሲጠቀሙ የኢቲሪየም አውታረ-መረብን ለመጠቀም በETH ክፍያ ይከፍላሉ። ይህ ክፍያ ለብሎክ ፕሮዲዩሰር እርስዎ ምን ለማድረግ እየሞከሩ እንደሆነ ፕሮሰስ እንዲያደርግና እንዲያረጋግጥ ማበረታቻ ነው።

ቫሊደተሮች የኢቲሪየም መዝገብ ጠባቂ ነገር ናቸው —ማንም እንዳያጭበረብር ይፈትሻሉ ይጠብቃሉ፡፡ የብሎክ ትራንዛክሽን ለማቅረብ በዘፈቀደ ይመረጣሉ፡፡ ይህን ስራ የሚሰሩ ቫሊዴተሮች በትንሽ መጠን አዲስ በመጣው ETH ይሸለማሉ።

ቫሊዴተሮች የሚሰሩት እና በቀብድ የሚያሲዙት ካፒታል ኢቲሪየምን ደህንነቱ የተጠበቀና ከማዕከላዊ ቁጥጥር ነፃ ያደርገዋል። ETH ለኢቴርየም ሀይል ይሰጣል

የእርስዎን ETH በቀብድ ሲያሲዙ፣ ኢቲሪየምን ለመጠበቅ ያግዛሉ ሽልማቶችንም ያገኛሉ። በዚህ ስርዓት, ETHን የማጣት ስጋት አጥቂዎችን ይከላከላል፡፡ ስለቀብድ ላይ ተጨማሪ

ETH የኢቲርየም ፋይናንስ ስርዓት መሰረት ነው

በክፍያዎች አልረኩም፣ የኢቲሪየም ማህበረሰብ የአቻ-ለአቻ እና ለሁሉም ተደራሽ የሆነ አጠቃላይ የፋይናንስ ስርዓት እየገነባ ነው።

በኢቲሪየም ላይ ሙሉ ለሙሉ የተለያዩ ክሪፕቶከረንሲ ለማመንጨት ETHን እንደ ማስያዣ መጠቀም ይችላሉ። በተጨማሪም በETH እና በETHን የሚደገፉ ቶከኖች መበደር፣ማበደር እና ወለድ ማግኘት ይችላሉ።

Wrapped ether (WETH) is used to extend the functionality of ETH to work with other tokens and applications. Learn more about WETH.

የETH ጥቅሞች በየቀኑ ያድጋሉ

ኢቲሪየም ፕሮግራመብል ስለሆነ ገንቢዎች ስፍር ቁጥር በሌላቸው መንገዶች ETHን ሊቀርጹ ይችላሉ።

ያኔ በ2015 ማድረግ የሚችሉት ነገር ቢኖር ETHን ከአንድ የኢቲሪየም አካውንተ ወደ ሌላ አካውንት መላክ ብቻ ነበር። ዛሬ ግን ልታደርጓቸው ከምትችሉት አንዳንድ ነገሮች እነሆ።

ለምንድን ነው ETH ዋጋ ያለው?

ETH ለተለያዩ ሰዎች በተለያዩ መንገዶች ጠቃሚ ነው።

ለኢቲሪየም ተጠቃሚዎች ETH ጠቃሚ የሆነበት ምክንያት የግብይት ክፍያዎችን እንዲከፍሉ ስለሚያደርግ ነው።

ሌሎች ደግሞ እንደ ዲጂታል ወርቅ አድርገው ይመለከቱታል ምክንያቱም አዲስ ETH መፍጠር በጊዜ ሂደት እየቀነሰ ይሄዳል፡፡

ከቅርብ ጊዜ ጀምሮ ETH በኢቲሪየም ላይ ላሉ የፋይናንስ መተግበሪያዎች ተጠቃሚዎች አስፈላጊ እየሆነ መጥቷል። ለክሪፕቶ ብድሮች ETHን እንደ ማስያዣ መጠቀም ወይም እንደ የክፍያ ሥርዓት መጠቀም ስለሚችሉ ነው።

በእርግጥ ብዙዎች እንደ ኢንቨስትመንት አድርገው ይመለከቱታል, ልክ እንደ ቢትኮይን ወይም ሌሎች ክሪፕቶ ምንዛሬዎች፡፡

ETH በኢቴርየም ላይ ብቸኛው ክሪፕቶ አይደለም

ማንኛውም ሰው አዲስ አይነት ንብረቶችን መፍጠር እና በኢቲሪየም ላይ መገበያየት ይችላል። እነዚህም 'ቶከኖች' በመባል ይታወቃሉ። ሰዎች ባህላዊ ገንዘቦችን፣ የማይንቀሳቀስ ንብረታቸውን፣ ኪነ ጥበባቸውን እና እራሳቸውን ጭምር በቶከን ወክለዋል!

ኢቲሪየም በሺዎች የሚቆጠሩ ቶከኖች መኖሪያ ነው - አንዳንዶቹ ከሌሎቹ የበለጠ ጠቃሚ እና ዋጋ አላቸው፡፡ ዴቨሎፐሮች አዳዲስ እድሎችን የሚከፍቱ እና አዳዲስ ገበያዎችን የሚከፍቱ አዳዲስ ቶከኖች በየጊዜው እየሰሩ ነው።

ተጨማሪ ነገሮች ስል ቶከኖች እና አጠቃቀማቸው

ታዋቂ የቶከን አይነቶች

ስቴብልኮይኖች

እንደ ዶላር አይነት የተለመዱ ምንዛሪዎች ዋጋ የሚያንፀባርቁ ቶከኖች። ይህም የአብዛኛዎችን የክሪፕቶ ምንዛሬዎች የዋጋ አለመረጋጋት ችግር ይፈታል።

የአስተዳደር ቶከኖች

ያልተማከለ ድርጅቶች ውስጥ ድምፅ መስጠትን አቅምን የሚወክሉ ቶከኖች።

መጥፎ ሳንቲሞች

አዳዲስ ቶከኖች መስራት ቀላል ስለሆነ ማንም ሰው ሊያደርገው ይችላል - መጥፎ ወይም የተሳሳተ ዓላማ ያላቸው ሰዎች እንኳን መስራት ይችላሉ፡፡ እነሱን ከመጠቀምዎ በፊት ሁልጊዜ ጥናት ያድርጉ!

መሰብሰብ የሚቻሉ ቶከኖች

የሚሰበሰብ ጨዋታ ንጥል፣ የዲጂታል ጥበብ ክፍል ወይም ሌላ ልዩ ንብረቶችን የሚወክሉ ቶከኖች። በተለምዶ የማይተኩ-ቶከኖች (NFTዎች) በመባል ይታወቃሉ።

Test your Ethereum knowledge

ይህ ገፅ አግዞዎት ነበር?