Skip to main content
የጀግና ETHን ምስል ያግኙ

ETHን የት ማግኘት ይቻላል

ETH ማግኘት፣ ከአቻዎችዎ መቀበል ወይም ከልውውጦች እና መተግበሪያዎች መግዛት ይችላሉ።


የአሁኑ ጊዜ የETH ዋጋ (በአሜሪካ ዶላር) 

በመጫን ላይ ነው...
(የመጨረሻ 24 ሰዓታት)
በአገር ይፈልጉ

የተማከሉ ምንዛሪዎች

ምንዛሬዎች በተለምዶ የምንጠቀመው ገንዘቦችን በመጠቀም ክሪፕቶ እንዲገዙ የሚያስችልዎ ንግዶች ናቸው ። በራሳችሁ ስር ወዳለ ቦርሳ እስክትልኩት ድረስ በምትገዙት ማንኛውም ETH ላይ ጥበቃ አላቸው ።

ETH ያግኙ

ለDAOs ወይም በcrypto ውስጥ ለሚከፍሉ ኩባንያዎች በመስራት፣ ጉርሻዎችን በማሸነፍ፣ የሶፍትዌር ስህተቶችን በማግኘት እና ሌሎችንም በማግኘት ETH ማግኘት ይችላሉ።

ከባልደረቦችህ ETH ን ተቀበል

አንዴ የ Ethereum መለያ ካሎት፣ የሚያስፈልጎት ነገር ቢኖር ETH (እና ሌሎች ቶከኖች) አቻ ለአቻ መላክ እና መቀበል ለመጀመር አድራሻዎትን ማጋራት ብቻ ነው።

ያልተማከሉ ምንዛሪዎች (DEXs)

If you want more control, buy ETH using . With a DEX you can trade digital assets without ever giving control of your funds to a centralized company.

ቦርሳዎች

አንዳንድ ቦርሳዎች ክሪፕቶ በዴቢት/ክሬዲት ካርድ፣ በባንክ ማስተላለፍ ወይም በApple Pay ጭምር እንዲገዙ ያስችሉዎታል። የቦታ ገደቦች ተፈጻሚ ይሆናሉ።

ሽልማቶችን ማሰባሰብ

ቀደም ሲል የተወሰነ ETH ካለዎት፣ አረጋጋጭ መስቀለኛ መንገድን በማስኬድ የበለጠ ገቢ ማግኘት ይችላሉ። ይህንን የማረጋገጫ ስራ በETH ውስጥ ለሰሩበት ክፍያ ይከፈለዎታል።

በዚህ ገጽ ላይ የተዘረዘሩት ሁሉም ምርቶች ይፋዊ ማረጋገጫዎች ሳይሆኑ ለመረጃ አገልግሎት ብቻ የቀረቡ ናቸው። አንድ ምርት መጨመር ወይም በፖሊሲው ላይ አስተያየት ለመስጠት ከፈለጉ በGitHub ውስጥ ጉዳይ ያንሱ። ችግር ያንሱopens in a new tab

በየትኛው ሀገር ነው የሚኖሩት?

የገንዘብ ልውውጦች crypto የት መሸጥ እንደሚችሉ ላይ ገደቦች አሏቸው። ይህ በእያንዳንዱ ሀገር ውስጥ ለመስራት የታሰበ አመላካች የአገልግሎቶች ዝርዝር ነው። እዚህ ተካተተ ማለት ማረጋገጫ አይደለም - የራስዎን ምርምር ማድረግ አለብዎት!

ያልተማከሉ ምንዛሪዎች (DEXs)

DEXዎች ምንድናቸው ?

ያልተማከሉ ምንዛሪዎች ለETH እና ለሌሎች ቶከኖች ክፍት የገበያ ቦታዎች ናቸው። ገዥዎችን እና ሻጮችን በቀጥታ ያገናኛሉ።

በግብይቱ ውስጥ ገንዘቦችን ለመጠበቅ የታመነ ሶስተኛ አካልን ከመጠቀም ይልቅ ኮድን ይጠቀማሉ። የሻጩ ETH ለገዢው የሚተላለፈው ክፍያ ሲረጋገጥ ብቻ ነው። ይህ ዓይነቱ ኮድ ዘመናዊ ውል በመባል ይታወቃል። ስለ ዘመናዊ ውሎች ተጨማሪ

ይህ ማለት ከማዕከላዊ አማራጮች ያነሰ የጂኦግራፊያዊ ገደቦች አሉ ማለት ነው፣ አንድ ሰው የሚፈልጉትን እየሸጠ ከሆነ እና እርስዎ ማቅረብ የሚችሉትን የመክፈያ ዘዴ ከተቀበለ፣ ዝግጁ ኖት ማለት ነው።

DEXን ለመጠቀም ቦርሳ ያስፈልግዎታል።

ቦርሳ ያግኙ

ሌላ ክሪፕቶ በመጠቀም ይግዙ

የእርስዎን ቶከኖችዎን በሌሎች ሰዎች ETH ይቀይሩ። እንዲሁም ተገላቢጦሹን ያድርጉ።

የእርስዎ ETHን ደህንነት የጠበቅ

Ethereum በየትኛውም ድርጅት ስር አይደለም - ያልተማከለ ነው።

ይህ ማለት የፈንድዎን ደህንነት በቁም ነገር ሊወስዱት ይገባል ማለት ነው። በETH የእርስዎን ንብረቶች ለመጠበቅ አንድ ባንክ ወይም ድርጅት ላይ እምነትዎን አይጥሉም፣ ለራስዎ ኃላፊነት ይወስዳሉ።

ETHዎን በግልዎ ዋሌት ውስጥ ያስቀምጡ

የግል ሂሳባችንን በማስተዳደር የራሳችን የሆነውን ንብረት አንድንቆጣጠር ማስቻሉ የEthereum ዋነኛ መገለጫ ነው። ይህም ማለት በግል ንብረቶቻችን ላይ ሌላ ሶስተኛ አካልን ማመን ሳይጠበቅብን በተጨማሪም ታማኝ ካልሆኑ ንብረት ጠባቂዎች ራሳችንን በመከላከል ከኪሳራ አና ከህገ ወጥ ጠላፊዎች ንብረታችንን ለመጠበቅ ያስችለናል። ነገር ግን የንብረታችንን ደህንነት ማረጋገጥ ሀላፊነት ሙሉ በሙሉ እኛ ላይ ይወድቃል ማለት ነው።

ቦርሳዎችን ይመልከቱ

የእርስዎ ETH አድራሻ

ቦርሳ ሲያወርዱ የእርስዎ የሆነ ይፋዊ የETH አድራሻ ይፈጥርልዎታል። ይህን ይመስላል:

0x0125e2478d69eXaMpLe81766fef5c120d30fb53f

ምሳሌ፡ ኮፒ አታድርጉት

ይህንን እንደ ኢሜል አድራሻዎ ያስቡ, ነገር ግን ከደብዳቤ ይልቅ ETH መቀበል ይችላል ። ETHን ከምንዛሬ ወደ ቦርሳዎ ማስተላለፍ ከፈለጉ አድራሻዎን እንደ መድረሻ ይጠቀሙ። ከመላክዎ በፊት ሁል ጊዜ በድጋሚ ማረጋገጥዎን እርግጠኛ ይሁኑ!

የቦርሳ መመሪያዎችን ይከተሉ

የመለያዎ መዳረሻ ከጠፈብዎ፣ የፈንድ መዳረሻዎን ያጣሉ። የእርስዎ ዋሌት ከዚህ ለመጠበቅ መመሪያዎችን ሊሰጥዎ ይችላል። በጥንቃቄ እነሱን መከተልዎን እርግጠኛ ይሁኑ - አብዛኛውን ጊዜ የመለያዎ መዳረሻ ከጠፋብዎ ማንም ሰው ሊረዳዎት አይችልም።

Page last update: 2 ጁላይ 2025

ይህ ገፅ አግዞዎት ነበር?