ኢቴርየምን ምንድን ነው?
እንደ ቢትኮይን ያሉ ክሪፕቶ ገንዘቦች ማንኛውም ሰው በዓለም አቀፍ ደረጃ ገንዘብ እንዲያስተላልፍ ያስችሉታል። ኢቲሪየም ይህን ነው የሚያደርገው፣ ግን በተጨማሪም ሰዎች መተግበሪያዎችን እና ድርጅቶችን እንዲፈጥሩ የሚያስችል ኮድ ማስኬድ ይችላል። እርሱም አስተማማኝ እና ተለዋዋጭ ነው፤ ማንኛውም ኮምፒተር ፕሮግራም በኢቲሪየም ላይ መካሄድ ይችላል። የበለጠ ይማሩ እና እንዴት መጀመር እንደሚችሉ ይወቁ፡
ኢቲሪየምን እንዴት መጠቀም አችላለው?
ኢቴርየምን መጠቀም ለብዙ ሰዎች የተለያየ ነገሮችን ሊያመለክት ይችላል። ምናልባት ወደ መተግበሪያ ለመግባት፣ የእርስዎን ማንነት ለማረጋገጥ ወይም የተወሰነ ETH ለማስተላለፍ ሊፈልጉ ይችላሉ። እርስዎ በመጀመርያ የሚያስፈልግዎት ነገር አካውንት ነው። አካውንት ለመክፈት እና ለመድረስ ቀላሉ መንገድ ዋሌት የተባለ መተግበርያን መጠቀም ነው።
ዋሌት ምንድን ነው?
ዲጂታል ዋሌቶች ልክ እንደ እውነተኛ ዋሌቶች ናቸው። ማንነትዎን ለማረጋገጥ እና ዋጋ የሚሰጡዋቸውን ቦታዎች መድረስ እንዲችሉ የሚፈልጉትን ያስቀምጣሉ።

ኢቴርየምን ሲጠቀሙ ከግምት ሊያስገቧቸው የሚገቡ ነገሮች
- አያንዳንዱ ኢቴሪይም ላይ የሚካሄዱ ግብይቶች የETH ክፍያን ይጠይቃሉ፣ ይህም ክፍያ ኢቴሪይምን አማክለው የተሰሩ ስቴብል ኮይኖችን ለምሳሌ USDC አና DAI የመሳሰሉት ላይ የሚደረጉትን ግብይቶችንም ያጠቃልላል።
- ኢቴርየምን ለመጠቀም በሚሞክሩ ሰዎች ብዛት ላይ በመመስረት ክፍያዎች ከፍተኛ ሊሆኑ ይችላሉ፣ ስለሆነም ይህን እንዲጠቀሙ እንመክራለን 2ኛው ንብርብር.

ኢቲሪየም ለምን ይጠቅማል?
ኢቴሪየም የኛን የኑሮ ሁኔታ በተለያየ መልኩ የሚያሻሽሉ ፈጠራዎችን ለመስራት አስችልዋል። ምንም እንኳን ገና ጅማሮ ላይ ቢሆንም በመጪው ምዕራፍ ግን ብዙ የሚያጓጉ ነገሮች ይኖራሉ።
ብቅ እያሉ ያሉ የአጠቃቀም ጉዳዮች
በተጨማሪም በኢቴሪየም አማካኝነት ዕውቅናን እያተረፉ ያሉ አዳዲስ ኢንዱስትሪዎች እየተፈጠሩ ሲሆን የነበሩት ደግሞ ራሳቸውን እያሻሻሉበት ይገኛሉ፡
የኢቲሪየምን አውታረ መረብን ማጠንከር
የእርስዎን ETH በማጠራቀም ኢቲሪየምን ለመጠበቅ እና በተመሳሳይ ጊዜ ሽልማቶችን ማግኘት ይችላሉ። እንደ ቴክኒካል እውቀትዎ እና ምን ያህል ETH እንዳለዎት በመለየት ለማካካስ የተለያዩ አማራጮች አሉ።
ስለ ኢቲሪየም ደንቦች ይማሩ
የኢቴሪየም አውታረ መረብ ሙያዊ ክፍል ላይ ልዩ ፍላጎት ላላቸው ተጠቃሚዎች።
የኢቲሪየም ፍኖተ ካርታ
የኢቲሪየም ፍኖተ ካርታ ኢቲሪየምን በከፍተኛ ሁኔታ እንዲያደርግ ያደርጋል፣ ደህንነቱ የተጠበቀ እና ዘላቂ እንዲሆን አስችሎታል።

ስለ ኢቲሪየም ማህበረሰብ ይወቁ
የኢቲሪየም ስኬት የተገኘው በማይታመን ሁኔታ ቆራጥ በሆነው ማህበረሰቡ ነው። በሺዎች የሚቆጠሩ የሚያበረታቱ እና ወደፊት እንድንሄድ የሚያደርጉ ሰዎች የኢቲሪየም ራዕይን ወደፊት እንዲገፋ ያግዛሉ፣ በተጨማሪም በማከማቸት እና በአስተዳደር ለአውታረ መረቡ ደህንነት ይሰጣሉ። ይምጡና ይቀላቀሉን!
የመስመር ላይ ማህበረሰቦች
በመስመር ላይ የሚገኘው ማህበረሰባችን የተለያዩ ጥያቄዎችን እንዲጠይቅ እንዲሁም ተሳትፎ እንዲያደርግ እድል ይሰጣል።

መጸሐፍት እና ፖድካስቶች
በኢቲሪየም ዙሪያ የተጻፉ መጽሃፍት
- The Cryptopians ፌብሩዋሪ 22፣ 2022 - ላውራ ሺን
- Out of the Ether ሴፕቴምበር 29፣ 2020 - ማቲው ሌይዚንግ
- The Infinite Machine ጁላይ 14, 2020 - ካሚላ ሩሶ
- Mastering Ethereum ዲሴምበር 23፣ 2018 - አንድሪያስ ኤም. አንቶኖፓውሎስ፣ ጋቭን ውድ ፒኤች.ዲ.
- Proof of Stake ሴፕቴምበር 13፣ 2022 - ቪታሊክ ቡተሪን፣ ናታን ሽናይደር
በኢቲሪየም ዙሪያ ያሉ ፖድካስቶች
- Green Pill ለዓለም አወንታዊ ውጫዊ ሁኔታዎችን የሚፈጥሩ የክሪፕቶ-ኢኮኖሚያዊ ስርዓቶችን ይቃኛል
- Zero Knowledge እያደገ ያለውን ያልተማከለ ድህረገጽንና ማህበረሰቡን የሚያንቀሳቅሰውን ቴክኖሎጂው በጥልቀት ይቃኛል
- Unchained ያልተማከለ በይነመረብን በሚገነቡ ሰዎች፣ የወደፊት ሕይወታችንን መሠረት ሊያደርጉ የሚችሉ የዚህ ቴክኖሎጂ ዝርዝሮች፣ እና በ kripto ውስጥ ካሉት እንደ ደንብ፣ ደህንነት እና ግላዊነት ያሉ በጣም አስጨናቂ ርዕሰ ጉዳዮችን በጥልቀት ይመለከታል።
- The Daily Gwei ስለኢተሪየም የዜና ማጠቃለያዎች፣ ወቅታዊ መረጃዎች እና ትንታኔዎች
- Bankless ስለ ክሪፕቶ ፋይናንስ አጋዥ መመሪያ