ወደ ዋናው ይዘት ይዝለሉ

Wanem ya Ethereum?

የእኛ ወደፊት ዲጂታል መሠረት

ኢቲሪየም እንዴት እንደሚሰራ፣ የሚያስገኛቸው ጥቅሞች እና በአለም ዙሪያ በሚሊዮኖች በሚቆጠሩ ሰዎች እንዴት ጥቅም ላይ እንደሚውል የተሟላ የጀማሪ መመሪያ።

አንድ ግለስብ ባዛር ውስጥ ሲያይ የሚያሳይ ምስል፣ ኢቴሪየምን ለመወከል ማለት ነው

Summary

ኢቲሪየም የኢቲሪየም ፕሮቶኮል ተብሎ የሚጠራውን ደንብ የሚከተሉ የአለም አቀፍ የኮምፒውተሮች መረብ ነው። የኢቴሬም አውታረ-መረብ ማንኛውም ሰው ሊገነባ እና ሊጠቀምባቸው ለሚችሉ ማህበረሰቦች፣ አፕሊኬሽኖች፣ ድርጅቶች እና ዲጂታል ንብረቶች መሰረት ሆኖ ይሰራል።

የኢቲሪየም አካዉንት ከየትኛውም ቦታ ሆነው በማንኛውም ጊዜ መፍጠር እና የመተግበሪያዎችን ዓለም ማሰስ ወይም የራስዎን መገንባት ይችላሉ። ዋናው ፈጠራ ህጎቹን ሊለውጥ ወይም መዳረሻዎን ሊገድብ የሚችል ማዕከላዊ ባለስልጣን ሳያምኑ ይህን ሁሉ ማድረግ ይችላሉ።

የበለጠ ለማወቅ ማንበብዎን ይቀጥሉ…ኢቴርየም ምን ማድረግ ይችላል?

🏦

የባንክ አገልግሎት ለሁሉም

ሁሉም ሰው የፋይናንስ አገልግሎት ማግኘት አይችልም ይሆናል። ነገር ግን ኢቲሪየምን እና በእሱ ላይ የተሰሩትን የማበደር፣ የመበደር እና የቁጠባ ምርቶች ጋር ለመድረስ የሚያስፈልግዎ የበይነ-መረብ ግንኙነት ብቻ ነው፡፡

🕵

ለሁሉም ክፍት የሆነ ኢንተርኔት

ማንኛውም ሰው ከኢቲሪየም አውታረ-መረብ ጋር መስተጋብር መፍጠር ወይም መተግበሪያዎችን መስራት ይችላል። ይህ በጥቂት ትላልቅ ኮርፖሬሽኖች ቁጥጥር ስር ከመሆን ይልቅ የእራስዎን ንብረቶችና ማንነት እንዲቆጣጠሩ ያስችልዎታል።

👥

የአቻ-ለአቻ አውታረ መረብ

ኢቲሪየም ዲጂታል ንብረቶችን በቀጥታ ከሌሎች ሰዎች ጋር ለማስተባበር, ስምምነት ለማድረግ ወይም ለማስተላለፍ ይፈቅድልዎታል። በመካከለኞች ላይ መተማመን አያስፈልግም።

🛡️

ሳንሱር የሚቋቋም

የትኛውም መንግስት ሆነ ኩባንያ ኢቲሪየምን መቆጣጠር አይችልም። በያልተማከለ አሰራር ማንም ሰው እርስዎን ክፍያ ከመቀበል ወይም በኢቲሪየም ላይ አገልግሎቶችን ከመጠቀም ሊያግድዎት አይችልም።

🛍️

የንግድ ዋስትናዎች

ደንበኞች የተስማሙበትን ካቀረቡ ብቻ ገንዘብ ወደ ሌላ እጅ የሚገባበት አስተማማኝና አብሮ የተገነባ ዋስትና አላቸው። በተመሳሳይም ገንቢዎች ደንቦቹ በእነሱ ላይ እንደማይለወጡ እርግጠኞች ሊሆኑ ይችላሉ።

🤝

መጣመር የሚችሉ ምርቶች

ሁሉም መተግበሪያዎች የተገነቡት ከሚጋሩ ግሎባል እስቴት ጋር በተመሳሳይ ብሎክቼይን ነው፣ ይህ ማለት እርስበርስ መገንባት ይችላሉ (እንደ ሌጎ ብሪክሶች)። ይህ የተሻሉ ምርቶችን እና ልምዶችን እና ማንም መተግበሪያዎች የሚተማመኑባቸውን መሳሪያዎች ማስወገድ እንደማይችሉ ማረጋገጫዎችን ይፈቅዳል።

ለምን ኢቴርየምን እጠቀማለሁ?

በአለምአቀፍ ደረጃ ለማስተባበር፣ ድርጅቶችን ለመፍጠር፣ መተግበሪያዎችን ለመገንባት እና ዋጋን ለመጋራት የበለጠ ተቋቋሚ፣ ክፍት እና ታማኝ መንገዶችን የሚፈልጉ ከሆነ ኢቲሪየም ለእርስዎ ነው። ኢቲሪየም በሁላችንም የተፃፈ ታሪክ ነው ፣ስለዚህ ኑ እና ከኢቲሪየም ጋር ምን አይነት አስደናቂ አለም መፍጠር እንደምንችል እንወቅ።

ከቁጥጥር ውጭ በሆኑ የውጭ ኃይሎች ምክንያት በንብረታቸው ደህንነት ወይም ጤናማነት ወይም ተንቀሳቃሽነት ላይ እርግጠኛ አለመሆንን ለተሸከሙ ሰዎች ኢቲሪየም እንዲሁ ከጠቃሚም በላይ ነው።

ርካሽ እና ፈጣን ድንበር ተሻጋሪ ክፍያዎች

ስቴብልኮይኖች ለዋጋው መሠረት በሆነ የተረጋጋ ንብረት ላይ የሚመረኮዝ አዲስ ክሪፕቶከረንሲ ዓይነት ነው። አብዛኛዎቹ ከዩናይትድ ስቴትስ ዶላር ጋር የተገናኙ ናቸው እና ስለዚህ የዶላር መገበያያ ገንዘብ ዋጋን ይጠብቃሉ፡፡ እነዚህ በጣም ርካሽ እና የተረጋጋ ዓለም አቀፍ የክፍያ ሥርዓት ይፈቅዳል፡፡ ብዙ የአሁኑ ጊዜ ስቴብልኮይኖች በኢቲሪየም አውታረ-መረብ ላይ የተገነቡ ናቸው።

ኢቲሪየም እና ስቴብልኮይኖች ወደ ውጭ አገር ገንዘብ የመላክ ሂደትን ቀላል ያደርገሉ። አማካይ ባንክዎን ሊወስድ ከሚችለው ከበርካታ የስራ ቀናት ወይም ሳምንታት በተቃራኒ ገንዘቦችን ወደ ዓለም ለማዘዋወር ጥቂት ደቂቃዎችን ብቻ ይወስዳል። በተጨማሪም፣ ከፍተኛ ዋጋ ላለው ግብይት ምንም ተጨማሪ ክፍያ የለውም፣ እና ገንዘብዎን የት እና ለምን እንደሚልኩ ላይ ምንም አይነት ገደቦች የሉም።

በችግር ጊዜ ፈጣኑ እርዳታ

በሚኖሩበት አከባቢ በሚታመኑ ተቋማት በኩል ብዙ የባንክ አማራጮችን ለማግኘት እድለኛ ከሆኑ፣ የሚያቀርቡትን የፋይናንስ ነፃነት፣ ደህንነት እና መረጋጋት እንደ ቀላል ነገር ሊወስዱት ይችላሉ። ነገር ግን በፖለቲካዊ ጭቆና ወይም በኢኮኖሚ ችግር ውስጥ ላሉ ብዙ ሰዎች የፋይናንስ ተቋማት የሚያስፈልጋቸውን ጥበቃ ወይም አገልግሎት ላይሰጡ ይችላሉ።

በቬንዙዌላ(opens in a new tab)ኩባ(opens in a new tab)አፍጋኒስታን(opens in a new tab)ናይጄሪያ(opens in a new tab)ቤላሩስ(opens in a new tab) እና ዩክሬን(opens in a new tab) ነዋሪዎች ላይ ጦርነት፣ ኢኮኖሚያዊ ውድመት ወይም የዜጎች ነፃነት ላይ ጥቃት ሲሰነዘር ክሪፕቶከረንሲዎች ፈጣን እና ብዙ ጊዜ የፋይናንስ ኤጀንሲን ለማቆየት ብቸኛ አማራጮች ናቸው። 1(opens in a new tab) በምሳሌዎቹ ላይ እንዳየነው፣ እንደ ኢቴሬም አይነት ክሪፕቶከረንሲዎች ሰዎች ከውጭው ዓለም ጋር ግኑኙነት ሲያጡ ያልተገደበ የዓለም አቀፍ ኢኮኖሚ መዳረሻን ሊሰጥ ይችላል፡፡ በተጨማሪም፣ በከፍተኛ ዋጋ ግሽበት ምክንያት የሀገር ውስጥ ገንዘቦች በሚወድቁበት ጊዜ የተረጋጋ ሳንቲም ዋጋ ማከማቻ ያቀርባሉ።

ፈጣሪዎችን ማበረታታት

በ2021 ብቻ አርቲስቶች፣ ሙዚቀኞች፣ ጸሃፊዎች እና ሌሎች ፈጣሪዎች 3.5 ቢሊዮን ዶላር አካባቢ ለማግኘት ኢቲሪየምን ተጠቅመዋል። ይህም ከSpotify፣ ከYouTube እና ከEtsy ጋር ኢቲሪየምን ለፈጣሪዎች ትልቅ አለማቀፍ መድረክ ከሚባሉት አንዱ ያደርገዋል። ተጨማሪ እወቅ(opens in a new tab)፡፡

ተጫዋቾችን ማበረታታት

ጨዋታዎችን ለማግኘት ይጫወቱ (ተጫዋቾች ጨዋታዎችን በመጫወት የሚሸለሙበት) በቅርቡ ብቅ እያሉና የጨዋታ ኢንዱስትሪውን እየቀየሩ ነው። በተለምዶ፣ በጨዋታ ውስጥ ያሉ ንብረቶችን በእውነተኛ ገንዘብ ለሌሎች ተጫዋቾች መገበያየት ወይም ማስተላለፍ የተከለከለ ነው። ይህ ተጫዋቾች ብዙውን ጊዜ የደህንነት ስጋት የሆኑትን የጥቁር ገበያ ድረ-ገጾችን እንዲጠቀሙ ያስገድዳቸዋል። በብሎክቼን ላይ ያለ ጨዋታ የውስጠ-ጨዋታ ኢኮኖሚን ያቀፈ እና እንደዚህ አይነት ባህሪን በታመነ መንገድ ያስተዋውቃል።

ከዚህም በላይ ተጫዋቾች በጨዋታ ውስጥ ቶከኖችን በእውነተኛ ገንዘብ በመገበያየት እናም ለጨዋታ ጊዜያቸው የእውነት ሽልማት በማግኘት ማበረታቻ ያገኛሉ።

2010
ባለሀብቶች
2014
ባለሀብቶች
ገንቢዎች
ኩባንያዎች
አሁን
ባለሀብቶች
ገንቢዎች
ኩባንያዎች
አርቲስቶች
ሙዚቀኞች
ጸሃፊዎች
ተጫዋቾች
ስደተኞች

ኢተርየም በቁጥር

4k+
Projects built on Ethereum
96M+
Accounts (wallets) with an ETH balance
53.3M+
Smart contracts on Ethereum
$410B
Value secured on Ethereum
$3.5B
Creator earnings on Ethereum in 2021
1.179 ሚ
Number of transactions today

ኢቲሪየምን የሚያስተዳድረው ማነው?

ኢቲሪየም በማንኛውም የተለየ አካል ቁጥጥር አይደረግበትም። የኢቲሪየም ፕሮቶኮልን ተከትለው ወደ ኢቲሪየም ብሎክቼን የሚጨምሩ ሶፍትዌሮችን የሚያንቀሳቅሱ የተገናኙ ኮምፒውተሮች ባሉበት ይኖራል። እያንዳንዳቸው እነዚህ ኮምፒውተሮች ኖድ በመባል ይታወቃሉ። እነዚህ ኖዶች በማንኛውም ሰው ሊንቀሳቀሱ ይችላሉ፣ ምንም እንኳን አውታረ መረቡን ለመጠበቅ ለመሳተፍ ETH (የኢቲሪየም የራስ ቶከን) በቀብድ ማስያዝ አለብዎት። 32 ETH ያለው ማንኛውም ሰው ፈቃድ ሳያስፈልገው ይህን ማድረግ ይችላል።

የኢቲሪየም ምንጭ ኮድ እንኳን በአንድ አካል አልተሰራም። ማንኛውም ሰው በፕሮቶኮሉ ላይ ለውጦችን መጠቆም እና ማሻሻያዎችን መወያየት ይችላል። በበርካታ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች በገለልተኛ ድርጅቶች የሚዘጋጁ የኢቴሬም ፕሮቶኮል በርካታ አተገባበርዎች አሉት፣ እና አብዛኛውን ጊዜ የሚገነቡት በክፍት ነው እና የማህበረሰብ አስተዋፅዖን ያበረታታሉ።

What are smart contracts?

የኢቲሪየም ምንጭ ኮድ እንኳን በአንድ አካል አልተሰራም። ማንኛውም ሰው በፕሮቶኮሉ ላይ ለውጦችን መጠቆም እና ማሻሻያዎችን መወያየት ይችላል። በበርካታ የፕሮግራሚንግ ቋንቋዎች በገለልተኛ ድርጅቶች የሚዘጋጁ የኢቴሪየም ፕሮቶኮል በርካታ አተገባበርዎች አሉት፣ እና አብዛኛውን ጊዜ የሚገነቡት በክፍት ነው እና የማህበረሰብ አስተዋፅዖን ያበረታታሉ።

የአገልግሎት ውሉ የለወጠ ምርት ተጠቅመው ያውቃሉ? ወይም ጠቃሚ ሆኖ ያገኙትን ባህሪ ተወግዶቦት ያውቃል? አንድ ዘመናዊ ውል ወደ ኢቲሪየም ከታተመ በኋላ፣ ኢቲሪየም እስካለ ድረስ በመስመር ላይ እና ተግባራዊ ይሆናል። ደራሲው እንኳን ሊያወርደው አይችልም። ዘመናዊ ውሎች አውቶማቲክ ስለሆኑ በማንኛውም ተጠቃሚ ላይ አድልዎ አያደርጉም እና ሁልጊዜ ለመጠቀም ዝግጁ ናቸው።

አበዳሪ መተግበሪያዎች፣ ያልተማከለ የንግድ ልውውጦች፣ ኢንሹራንሾች፣ ኩዋድራቲክ የገንዘብ ድጋፍ፣ ማህበራዊ አውታረ መረቦች፣ NFTዎች - በእርስዎ አእምሮ ያሉ ሌላ ነገሮች ጭምር የዘመናዊ ውሎች ታዋቂ ምሳሌዎች ናቸው።

ስለ ዘመናዊ ውሎች ተጨማሪdappዎችን ይመልከቱ

Etherን፣ የኢቲሪየምን ክሪፕቶከረንሲ ያግኙ

በኢቲሪየም አውታረ-መረብ ላይ ያሉ ብዙ ድርጊቶች በኢቲሪየም ኢምቤድድ ኮምፒውተር (ኢቴሪየም ቨርቹዋል ማሽን በመባል የሚታወቁት) አንዳንድ ስራዎች እንዲሰሩ ይጠይቃሉ። ይህ ስሌት ነፃ አይደለም; Ether (ETH) የተባለውን የኢቲሪየም የራሱ ክሪፕቶከረንሲ በመጠቀም ይከፈላል። ይህ ማለት አውታረ-መረቡን ለመጠቀም ቢያንስ አነስተኛ መጠን ያለው Ether ያስፈልግዎታል ማለት ነው።

Ether ሙሉ ለሙሉ ዲጂታል ነው፣ እና ወደ ማንኛውም የአለም ክፍል በቅጽበት መላክ ይችላሉ። የEther አቅርቦት በማንኛውም መንግስት ወይም ኩባንያ ቁጥጥር ስር አይደለም - ያልተማከለ እና ሙሉ በሙሉ ግልጽ ነው። Ether የሚሰጠው በፕሮቶኮሉ መሰረት ትክክለኛ በሆነ መንገድ ነው፣ አውታረ-መረቡን ለሚጠብቁ ባለድርሻዎች ብቻ ነው።

የኢቲሪየም የኃይል ፍጆታስ?

በሴፕቴምበር 15፣ 2022፣ ኢቲሪየም በውህደት ማሻሻያ በኩል አልፏል፣ ይህም ኢቲሪየምን ከስራ ማረጋገጫ ወደ ቀብድ ማረጋገጫነት ያሸጋገረ ነው።

ውህደቱ የኢቲሪየም ትልቁ ማሻሻያ ነበር እና ኢቲሪየምን ለመጠበቅ የሚያስፈልገውን የኃይል ፍጆታ በ99.95% በመቀነሱ በጣም አነስተኛ የካርበን ወጪ የበለጠ ደህንነቱ የተጠበቀ አውታረ መረብ ይፈጥራል። ኢቴሬም በአሁኑ ጊዜ አነስተኛ-የካርቦን ብሎክቼይን ሲሆን ደህንነቱን እና መጠኑን ከፍ ያደርገዋል.

ክሪፕቶ ለወንጀለኛ ተግባር መሳሪያነት ጥቅም ላይ እንደሚውል ሰምቻለሁ። ይህ እውነት ነው?

እንደ ማንኛውም ቴክኖሎጂ, አንዳንድ ጊዜ አላግባብ ጥቅም ላይ ይውላል። ነገር ግን፣ ሁሉም የኢቲሪየም ግብይቶች ክፍት በሆነው ብሎክቼን ላይ ስለሚፈጸሙ፣ ባለሥልጣኖች በተለመደው የፋይናንስ ሥርዓት ውስጥ ካለው ይልቅ ሕገወጥ እንቅስቃሴን መከታተል ቀላል ይሆንላቸዋል።

በቅርቡ የአውሮፓ ህብረት የህግ ማስከበር ትብብር ኤጀንሲ፣ Europol ባወጣው ቁልፍ ግኝቶች መሰረት ክሪፕቶ ለወንጀል ዓላማ ከገንዘብ ኖት ምንዛሬዎች በጣም ባነሰ ሁኔታ ጥቅም ላይ ይውላል።

"የክሪፕቶከረንሲዎችን ለህገወጥ ተግባራት መጠቀም ከአጠቃላይ ክሪፕቶ ኢኮኖሚ ትንሽ ክፍልን ብቻ ያቀፈ ይመስላል፣ እና በተለመደው ፋይናንስ ውስጥ ካለው ህገወጥ የገንዘብ መጠን አንፃር ሲታይ ደግሞ አነስተኛ ይመስላል።"

የኢቲሪየምና የቢትኮይን ልዩነት ምንድን ነው?

በ2015 የጀመረው ኢቴሬም ከአንዳንድ ትልቅ ልዩነቶች ጋር በቢትኮይን ፈጠራ ላይ የተገነባ ነው።

ሁለቱም ዲጂታል ገንዘብ ያለክፍያ አቅራቢዎች ወይም ባንኮች እንዲጠቀሙ ያስችሉዎታል። ግን ኢቲሪየም በፕሮግራም የሚደረግ ነው፣ ስለዚህ ያልተማከሉ መተግበሪያዎችን በአውታረ-መረቡ ላይ መገንባት እና መልቀቅ ይችላሉ።

ቢትኮይን ዋጋ አለው ብለን ስለምናስበው መሠረታዊ መልእክት እርስ በርሳችን እንድንላላክ ያስችለናል። ያለ ሥልጣን ዋጋ ማቋቋም በራሱ ትልቅ ነገር ነው። ኢቴሪየም ይህንን ወደ ሌላ ርቀት ይወስደዋል፡ ከመልእክቶች ብቻ ይልቅ ማንኛውንም ፕሮግራም ወይም ውል መፃፍ ይችላሉ። ሊፈጠሩ እና ሊስማሙ በሚችሉ የኮንትራቶች ዓይነት ላይ ምንም ገደብ የለም ፣ ስለሆነም ታላቅ ፈጠራ በኢቲሪየም አውታረ መረብ ላይ ይከሰታል።

ቢትኮይን የክፍያ አውታረ-መረብ ብቻ ሲሆን, ኢቲሪየም ግን እንደ የፋይናንስ አገልግሎቶች, ጨዋታዎች, ማህበራዊ አውታረ-መረቦች እና ሌሎች መተግበሪያዎች የገበያ ቦታ ነው፡፡

Further reading

የሳምንት የኢቲሪየም ዜና(opens in a new tab) - በሥነ-ምህዳር ዙሪያ ያሉ ቁልፍ እድገቶችን የሚሸፍን ሳምንታዊ ጋዜጣ።

አቶሞች፣ ተቋማት፣ብሎክቼይኖች(opens in a new tab) ብሎክቼን ለምን አስፈላጊ ነው?

ከርነል(opens in a new tab) የኢቲሪየም ህልም

ኤቲሪየምን ይጎብኙ

Test your Ethereum knowledge

Loading...

ይህ ገፅ አግዞዎት ነበር?