ወደ ዋናው ይዘት ይዝለሉ
የወደፊት የከተሞችን ነጸብራቅ የሚወክል የኢቲሪየም ስነ ምህዳር ነው።

ወደ ኢቴሪየም እንኳን ደህና መጡ

ኤቲሪየም የክሪፕቶከረንሲ ኤተር (ETH) እና በሺዎች የሚቆጠሩ ያልተማከሉ መተግበሪያዎች የሚንቀሳቀስና በማህበረሰብ የሚተዳደር ቴክኖሎጂ ነው።.

ኤቲሪየምን ይጎብኙ

ጀምር

ethereum.org ወደ ኤቲሪየም አለም ውስጥ የእርስዎ የመግቢያ በር ነው። ቴክኖሎጂው አዲስ እና በየጊዜው እየተሻሻለ የሚገኝ ነው – መመሪያዎችን ለማግኘት ይረዳል። በጥልቀት ለመረዳት ከፈለጋችሁ ምን ማድረግ እንዳለባችሁ በምክረ ሃሳብ እናበረታታሃለን።.
ኮምፒውተር ላይ የሚሠራ ሰው ምስል.

Wanem ya Ethereum?

ኤቴሪየም የዲጂታል ገንዘብ፣ ዓለም አቀፍ ክፍያዎች፣ እና መተግበሪያዎች መኖሪያ የሆነ ቴክኖሎጂ ነው። የዲጂታል ኢኮኖሚ፣ ፈጣሪዎች በኢንተርኔት አማካኝነት ገቢ የሚያገኙባቸውን ልዩ ፈጠራን ድፍረት የተሞላበት አዳዲስ መንገዶችና ሌሎች ብዙ ነገሮች የገነባ ለሁሉም ክፍት የሆነ የዲጅታል ማህበረስብ ነው። በየትኛውም የአለም ክፍል ሁኖ መሳተፍ ይቻላል – የሚያስፈልግህ ኢንተርኔት ብቻ ነው።.
Wanem ya Ethereum?በዲጂታል ገንዘብ ላይ ተጨማሪ መረጃ
ኤተሪየምን አስመልክቶ በተዘጋጀ ባዛር አንድ ግለስብ በመስኮት አፍጦ ሲያይ የሚያሳይ ምስል.

ፍትሐዊ የሆነ የገንዘብ ሥርዓት

ዛሬ በቢሊዮን የሚቆጠሩ ሰዎች የባንክ ሂሳብ መክፈት አይችሉም። ሌሎች ደግሞ ክፍያቸው ተዘግቷል። የ ኤተሪየም ያልተማከለ የገንዘብ ስርዓት ፈጽሞ የማይተኛ አድልዎ የሌለው ወይም የማያጋጥመውም የዲጅታል ፋይናንስ ስርዓት ነው። በኢንተርኔት ግንኙነት ብቻ፣ በየትኛውም የዓለም ክፍል ገንዘብ መላክ፣ መቀበል፣ መበደር፣ ወለድ ልታገኝና አልፎ ተርፎም ገንዘብን ወደ አንድ አካባቢ ልትጎርፍ ያስችላል።.
የ ETH ምልክት የሚያቀርቡ እጆች ምስል.

የንብረቶች ኢንተርኔት

ኤተሪየም ዲጅታል ገንዘብ ብቻ አይደለም። እርስዎ ያሎት ማንኛውንም ነገር ሊወከሉ፣ ሊነግዱ እና በቀላሉ ተተኪ ቅጂ ያልሆኑ ተምሳሌቶችን (NFTs) መጠቀም ይችላሉ። የኪነ ጥበብህን ስራዎችን ወደ ምልክቶች(ቶከንስ) መቀየር ትችላለህ በድጋሚም በሸጠህ ቁጥር የባለቤትነት ገቢ ማግኘት ትችላለህ። ወይም ደግሞ ያለህን ምልክት(ቶከን) ተጠቅመህ ብድር ለመበደር ያስችልሃል። አማራጮቹ በየጊዘው እየጨመሩ ነው.
በሆሎግራም አማካኝነት የሚታየው የETH አርማ.

ለሁሉም ክፍት የሆነ ኢንተርኔት

ዛሬ የግል መረጃዎቻችንን አሳልፈን በመስጠት " ነፃ'' የኢንተርኔት አገልግሎቶችን ማግኘት እንችላለን። ኤተሪየም አገልግሎቶች በስነተግባሮት ክፍት ናቸው – አገልግሎቱን ለመጠቀም የሚያስፈልግዎት የኢ ቦርሳ ብቻ ነው። ይህንንም በነጻ እና በቀላሉ ማዘጋጀት፣ በእርስዎ ቁጥጥር፣ እና ያለ ምንም የግል ኢንፎርሜሽን ማጋራት ይሰራሉ።.
በኤተሪየም ክሪስታሎች የሚንቀሳቀሰው የወደፊቱ ኮምፒውተር የሚያሳይ ምስል.
የኮድ ምሳሌዎች
የግልዎ ባንክ
ፕሮግራም ባደረጉት አካሄድ የጎለበተ ባንክ መገንባት ይችላሉ።
የራስህ መገበያያ ገንዘብ
በመተግበሪያዎች ላይ ማዛወር እና መጠቀም የሚያስችሉ ቶከኖችኝ መፍጠር ይችላሉ።.
የጃቫስክሪፕት ኤተሪየም የኢ ቦርሳ
ከኤተሪየም እና ሌሎች መተግበሪያዎች ጋር ግንኙነት ለማድረግ አሁን ያሉ ቋንቋዎችን መጠቀም ይችላሉ።.
ክፍት, ፈቃድ የሌለው DNS
እንዳልተማከለ ስርዓት አሁን ያሉ አገልግሎቶችን እና፣ ክፍት መተግበሪያዎች እንደገና መገመት ይችላሉ።.

የወደፊቱና አዲሱ የልማት ድንበር

ኤተሪይም እና መተግበሪያዎቹ ግልፅ እና ክፍት ምንጮች ናቸው። እርስዎ የ fork ኮድ እና ሌሎች አስቀድመው የገነቡትን አሰራር ዳግም መጠቀም ይችላሉ። አዲስ ቋንቋ መማር ካልፈለጋችሁ ጃቫ ስክሪፕት እና ሌሎች ያሉ ቋንቋዎችን በመጠቀም ክፍት ከሆኑ ኮዶች ጋር መገናኘት ትችላላችሁ።.

ኤቴሪየም ዛሬ

የቅርብ ጊዜ አውታረ መረብ ስታቲስቲክስ

ጠቅላላ በቀብድ የተያዘው ኢት

አጠቃላይ የETH መጠን በአሁኑ ጊዜ በቀብድ ተይዞ እና የአውታረ መረቡን ደህንነት እየጠበቀ ይገኛል።

32.76 ሚ

የዛሬ ጊዜ የንግድ ልውውጥ

ባለፉት 24 ሰዓታት ውስጥ በአውታረ መረብ ላይ በተሳካ ሁኔታ የተሰሩ የንግድ ልውውጦች ብዛት.

1.128 ሚ

በ DeFi የተቆለፈ ዋጋ(USD)

ባልተማከለ ፋይናንስ (DeFi) መተግበሪያዎች ውስጥ የገንዘብ መጠን፣ የኤቲሪየም ዲጂታል ኢኮኖሚ።.

US$134.3 ቢ

ቅርንጫፎች

ኤተሪየም በዓለም ዙሪያ በብዙ ሺህ የሚቆጠሩ ፈቃደኛ ሠራተኞች የሚተዳደር ሲሆን እነዚህ ፈቃደኛ ሠራተኞች ቅርንጫፎች (Nodes) በመባል ይታወቃሉ።.

5,943

የEthereum.org ማህበረሰብን ይቀላቀሉ

ወደ 40 000 የሚጠጉ አባላትን በDiscord ሰርቨራችን(opens in a new tab) ይቀላቀሉ፡፡

የEthereum.org ልማትና ጠቃሚ የስነ-ምህዳር ዜናዎች ላይ አስደሳች ማሳወቂያዎችን ለማግኘት የእኛ የወርሃዊ ማህበረሰብ ጥሪን ይቀላቀሉ፡፡ ጥያቄዎችን ለመጠየቅ፣ ሀሳቦችን ለማጋራት እና አስተያየት ለመስጠት እድሉን ያግኙ - ይህም የበለጸገ የኢትሪየም ማህበረሰብ አካል ለመሆን የተመቻቸ እድል ነው፡፡

☎️ Ethereum.org Community Call - June 2024

27 ጁን 2024 15:00

(UTC)

Join Discord(opens in a new tab)ወደ ቀን መቁጠሪያ አክል(opens in a new tab)

መጪ ጥሪዎች


መጪ ጥሪዎች የሉም

ቀዳሚ ጥሪዎች


20 ጁን 2024

Ethereum.orgን ይጎብኙ