ወደ ዋናው ይዘት ይዝለሉ

የኢቴርየም ቦርሳዎች

ለዲጂታል ወደፊቶ ቁልፍዎን ይያዙ

ቦርሳዎች እርስዎን ከዲጂታል ንብረቶችዎ ጋር የሚያገናኙ ሲሆኑ ወደ መተግበሪያዎች እንዲገቡ ያግዙዎታል።.

የኢቴሪየም ቦርሳን የሚወክል ሰውነቱ ላይ ካዝና ያለው ሮቦት ምስል

የኢቴርየም ቦርሳ ምንድነው?

የኢቴርየም ቦርሳዎች ሒሳብዎን እንዲቆጣጠሩ የሚያስችልዎ መተግበሪያዎች ናቸው ። ልክ እንደ አካላዊ ቦርሳዎት፣ ማንነትዎን ለማረጋገጥ እና ንብረትዎን ለመቆጣጠር የሚያስፈልጎትን ነገር ሁሉ አካቶ ይዟል። ቦርሳዎ ወደ መተግበሪያዎ እንዲገቡ ፣ ቀሪ ሂሳብዎን እንዲያውቁ፣ ግብይቶችን እንዲፈጽሙ እና ማንነትዎን እንዲያረጋግጡ ያስችሎታል።

አብዛኞቹ ሰዎች ዲጂታል ንብረታቸውን እና ማንነታቸውን ለመቆጣጠር ቦርሳዎችን ይጠቀማሉ።

ቦርሳዎ ከኢቴርየም አካውንቶ ጋር ለመገናኘት የሚያገለግል መሳርያ ነው፡፡ ይህም ማለት በማንኛውም ጊዜ የቦርሳ አቅራቢዎን መለወጥ ይችላሉ:: ብዙ ቦርሳዎች ከአንድ መተግበሪያ ብዙ የኢቴርየም ሒሳቦችን ለመጠቀም ያስችሉዎታል።

ቦርሳ አቅራቢዎች በገንዘብዎ ላይ ስልጣን የላቸውም። በኢቲሪየም ላይ ያሉትን ንብረቶቻችሁን መመልከቻ መስኮት እና በቀላሉ የሚያስተዳድሩባቸውን መሳሪያዎች ማቅረብ እንጂ።

ገንዘብዎን ለማስተዳደር የሚያስችል መተግበሪያ

ቦርሳዎ ቀሪ ሒሳቦችዎን፣ የግብይት ታሪክዎን ያሳያል እንዲሁም ገንዘብ ለመላክ/ለመቀበል መንገድ ይሰጥዎታል። አንዳንድ ቦርሳዎች ተጨማሪ ነገሮችንም ሊያቀርቡ ይችላሉ።

የእርስዎ የኢቲርየም ሒሳብ

የእርስዎ ቦርሳ ለኢቲሪየም ሂሳቦ – ለቀሪ ሂሳቦ፣ ለትራንዛክሽን ታሪኮ እና ተጨማሪ ማህደሮ መስኮት ነው፡፡ ነገር ግን በማንኛውም ጊዜ የቦርሳ አቅራቢዎችን መቀየር ይችላሉ፡፡

ወደ ኢቴርየም መተግበሪያ መግቢያዎ

ቦርሳዎ የኢቴርየም ሒሳብዎን በመጠቀም ከመተግበሪያዎች ጋር እንዲገናኙ ያስችልዎታል። ልክ ብዙ መተግበሪያዎችን መጠቀም እንደሚያስችል መግቢያ ነው።

ቦርሳዎች ፣ ሒሳቦች ፣ ቁልፎች እና አድራሻዎች

በአንዳንድ ቁልፍ ቃላት መካከል ያለውን ልዩነት መረዳት ተገቢ ነው።

  • የኢቴሬም ሒሳብ ልክ እንደ ጥንድ ቁልፎች ነው፣ አንደኛው ቁልፍ ሒሳብ ለመክፈት የሚያገለግል ሲሆን እንደልብ ሊያጋሩት ይችላሉ፣ ሌላኛው ግን ነገሮችን ለመፈረም ስለሚያገለግል በሚስጥር ሊጠብቁት ይገባል። እነዚህ ቁልፎች አንድ ላይ ሆነው ንብረቶችን ለመያዝ እና ግብይቶችን ለመፈጸም ያስችሉዎታል።

  • እያንዳንዱ የኢቴሪየም ሒሳብ የራሱ አድራሻ አለው፣ ልክ በኢሜይል የተላከ ደብዳቤ ልዩ ኢሜይል አድራሻ እንደአለው ሁሉ። ይህ የእርስዎን ዲጂታል ንብረቶች ለመለየት ጥቅም ላይ ይውላል።

  • ቦርሳ ቁልፎችዎን በመጠቀም ከሒሳብዎ ጋር እንዲገናኙ የሚያስችል መሳሪያ ነው ። ቦርሳዎ ቀሪ ሂሳብዎን እንዲያውቁ፣ ግብይቶችን እንዲፈጽሙ እና ሌሎች ተጨማሪ ነገሮችን እንዲያደርጉ ያስችሎታል።

አብዛኛዎቹ የቦርሳ ስሪቶች የኢቴርየም ሒሳብ እንዲከፍቱ ያስችሉዎታል። ስለዚህ ቦርሳ ከማውረድዎ በፊት ሒሳብ መክፈት አያስፈልግዎትም።

የቦርሳ አይነቶች

ለሒሳብዎ የፊት ገጽ ለመስጠት እና ከሒሳብዎ ጋር ለመገናኘት ጥቂት መንገዶች አሉ:

ሀርድ ዌር ቦርሳዎች ያለ ኢንተርኒት ግንኙነት የእርስዎን ክሪፕቶ እንዲያቆዩ የሚያስችልዎ መሳሪያዎች ናቸው - ደህንነታቸው በጣም የተጠበቀ

ከየትኛውም ቦታ ሆነው ገንዘብዎን ተደራሽ የሚያደርጉበት የሞባይል መተግበሪያዎች

የድረገጽ ማሰሻ ቦርሳዎች የድረገጽ መተግበሪያዎች ሲሆኑ ሒሳብዎን ከድረገጽ ማሰሻ በቀጥታ እንዲገናኙ ያስችልዎታል

የድረገጽ ማሰሻ ቅጥያ ቦርሳዎች ከሂሳቦ እና ከመተግበሪያዎች ጋረ መገናኘት የሚያስችሉ በድረገጽ ማሰሻ በኩል የሚጫኑ ቅጥያዎች ናቸው

ገንዘብዎን በmacOS፣ በWindows ወይም በLinux ላይ በመጠቀም ማስተዳደር ከፈለጉ የሚጫኑ የዴስክቶፕ መተግበሪያዎች

ቦርሳዎችን በባህሪያቸው መሰረት ያወዳድሩ

እርስዎ በሚፈልጉት ባህሪያት ላይ በመመስረት ቦርሳዎን እንዲመርጡ ልንረዳዎ እንችላለን።
ቦርሳ ያግኙ

ደህንነትን እንዴት መጠበቅ እንደሚቻል

የፋይናንስ ነፃነት እና በየትኛውም ቦታ ገንዘብን ማግኘት እና መጠቀም መቻል ከኃላፊነት ጋር አብሮ ይመጣል - በክሪፕቶ ውስጥ ለደንበኛ ድጋፍ ብሎ ነገር የለም። የቁልፎችዎን ደህንነት በጥንቃቄ የመጠበቅ ሃላፊነት የእርስዎ ነው።

ለገንዘብዎ ሃላፊነት ይውሰዱ

የተማከሉ ምንዛሪዎች ቦርሳዎን መልሰው ለማግኘት ይችሉ ዘንድ በተለምዶ የተጠቃሚ ስምን ከይለፍ ቃል ጋር አገናኝተው ያስቀምጣሉ። ገንዘብዎን በምንዛሪ ጥበቃ ስር ማስቀመጥዎን ያስታውሱ። እንደ ድንገት ምንዛሪው ችግር ካጋጠመው፣ የእርስዎ ገንዘቦች ለአደጋ ይጋለጣሉ።

የሚስጥር ሐረግዎን ይፃፉ

ቦርሳዎች አብዛኛውን ጊዜ በአስተማማኝ ቦታ መፃፍ ያለብዎትን የሚስጥር ሐረግ ይሰጡዎታል። ቦርሳዎን መልሰው ማግኘት የሚችሉት በዚህ መንገድ ብቻ ነው።

ይህን ምሳሌ እንመልከት:

there aeroplane curve vent formation doge possible product distinct under spirit lamp

በኮምፒተር ላይ አያስቀምጡት። ይፃፉ እና በጥንቃቄ ይያዙት።

ቦርሳዎ ላይ ምልክት ያስቀምጡ

የድረገጽ ቦርሳን የሚጠቀሙ ከሆነ፣ ከአጭበርባሪዎች ራስዎን ለመጠበቅ ድረገጹ ላይ የማስታወሻ ምልክት ያስቀምጡ።

ሁሉንም ነገር ሶስት ጊዜ ደጋግመው ያረጋግጡ

ግብይቶችን ወደ ኋላ መመለስ እና የጠፉ ቦርሳዎችን በቀላሉ መልሶ ማግኘት እንደማይቻል ያስታውሱ ስለዚህ ሁልጊዜ ጥንቃቄ ያድርጉ።

ደህንነትን ስለመጠበቅ ተጨማሪ ምክሮች

ከማህበረሰቡ

ኤቲሪየምን ይጎብኙ

Test your Ethereum knowledge

ይህ ገፅ አግዞዎት ነበር?