ወደ ዋናው ይዘት ይዝለሉ

የማይተኩ ቶከኖች (NFT)

  • ማንኛውንም ልዩ የሆነ ነገር የሚወከልበት መንገድ እንደ ኢቴሪየም-ተኮር ንብረት።
  • NFTዎች ከበፊቱ በበለጠ ለይዘት ፈጣሪዎች የበለጠ ኃይል እየሰጡ ነው።
  • በኢቲሪየም ብሎክቼን ላይ በዘመናዊ ውሎች የጎለበቱ።

NFTዎች ምንድናቸው?

እያንዳንዳቸው NFTዎች ልዩ የሆኑ ቶከኖች ናቸው። እያንዳንዱ NFT የተለያዩ ንብረቶች አሉዋቸው (የማይተኩ) እና በጣም በትንሽ ብዛት ይገኛሉ። ይህም ከእንደ ERC-20 ቶከኖች እያንዳንዱ ሚመሳሰሉ በአንድ ስብስብ ውስጥ እንዳሉ ቶከኖች ከተመሳሳይ ባህሪያት ካላቸው ('የሚተኩ') ይለያል። በቦርሳህ ውስጥ የትኛው የተለየ የዶላር ገንዘብ እንዳለህ ግድ አይልህም፣ ምክንያቱም ሁሉም ተመሳሳይ እና ዋጋቸው አንድአይነት ነው። ነገር ግን፣ እርስዎ የየትኛው NFT ባለቤት እንደሆኑ ይጨነቃሉ፣ ምክንያቱም ሁሉም ከሌሎች የሚለያቸው ('የማይተካ') የግል ንብረቶች ስላሏቸው ነው።

የእያንዳንዱ NFT ልዩነት እንደ ስነ ጥበብ፣ ተሰብሳቢ ነገሮች ወይም ሪል እስቴት ያሉ ነገሮችን በቶከን መወከል ያስችላል፣ አንድ ልዩ NFT የተወሰነ ልዩ እውነተኛ ዓለም ወይም ዲጂታል ንጥል ነገርን ይወክላል። የንብረት ባለቤትነት በኢቲሪየም ብሎክቼን የተጠበቀ ነው - ማንም ሰው የባለቤትነት መዝገብን ማሻሻል ወይም አዲስ NFT ገልብጦ/ለጥፎ ወደ ማኖር ማድረግ አይችልም።

የንብረቶች በይነ መረብ

NFT እና ኢቲሪየም በአሁኑ ጊዜ በይነመረብ ላይ ያሉትን አንዳንድ ችግሮች ይፈታሉ፡፡ ሁሉም ነገር ዲጂታል እየሆነ ሲመጣ የአካላዊ ንጥሎችን እንደ እጥረት፣ ልዩነት እና የባለቤትነት ማረጋገጫ ያሉ ባህሪያት የማባዛት ፍላጎት ይጨምራል። በማዕከላዊ አካል ቁጥጥር ስር ባልሆነ መንገድ። ለምሳሌ NFTዎችን በመጠቀም በአንድ በተወሰነ ኩባንያ የሙዚቃ መተግበሪያ ላይ ያልተወሰነ የmp3 የሙዚቃ ባለቤት መሆን ይችላሉ ወይም በመድረክ አቅራቢው በዘፈቀደ ከእርስዎ ሊወሰድ የማይችል ፣ መሸጥ ወይም መቀየር የሚችሉት የማህበራዊ ሚዲያ መያዣ ስም ባለቤት መሆን ይችላሉ ።

ዛሬ ብዙዎቻችን የምንጠቀመው በይነ መረብ ከNFTዎች በይነ መረብ ጋር ሲወዳደር ምን እንደሚመስል እነሆ...

ንጽጽር

የNFT በይነ መረብየዛሬው በይነ መረብ
የንብረቶችዎ ባለቤት ነዎት! መሸጥ ወይም መቀየር የሚችሉት እርስዎ ብቻ ነዎት።ከአንዳንድ ድርጅት ንብረት ይከራያሉ።
NFTዎች የዲጂታል ልዩነት አላቸው፣ ሁለት NFTዎች መቼም አንድ አይደሉም።የአንድን ስራ ቅጂ ብዙውን ጊዜ ከዋናው ስራ መለየት አይቻልም።
የNFT ባለቤትነት በማንም ሰው እንዲረጋገጥ በብሎክቼይን ላይ ይቀመጣል።የዲጂታል እቃዎች ባለቤትነት መዝገቦች በተቋማት ቁጥጥር ስር ባሉ ሰርቨሮች ላይ ተቀምጠዋል - የእነሱን ቃል ማመን አለብዎት።
NFTዎች በኢቲርየም ላይ ያሉ ዘመናዊ ውሎች ናቸው። ይህ ማለት በኢተርየም ላይ ባሉ ሌሎች ዘመናዊ ውሎች እና መተግበሪያዎች ውስጥ በቀላሉ ጥቅም ላይ ሊውሉ ይችላሉ!የዲጅታል ምርቶች ያላቸው ኩባንያዎች አብዛኛውን ጊዜ የራሳቸው "የታጠረ" መሠረተ ልማት ያስፈልጋቸዋል።
የሚድያ ስራ ፈጣሪዎች ስራቸውን በየትኛውም ቦታ መሸጥ እና አለምአቀፍ ገበያ ማግኘት ይችላሉ።ፈጣሪዎች በሚጠቀሙባቸው መድረኮች መሠረተ ልማት እና ስርጭት ላይ ይወሰናሉ። እነዚህ ብዙውን ጊዜ በአጠቃቀም ውሎች እና በጂኦግራፊያዊ ገደቦች ስር ተገዢ ናቸው።
የNFT ፈጣሪዎች በራሳቸው ስራ ላይ የባለቤትነት መብቶችን ይዘው መቆየት እና የሮያሊቲ ክፍያን በቀጥታ በNFT ውል ማስገባት ይችላሉ።እንደ የሙዚቃ ማሰራጫያ ያሉ አገልግሎቶችን የሚያቀርቡ መድረኮች ከሽያጮች የሚገኘውን አብዛኛው ትርፍ ያወስዳሉ።

NFTዎች እንዴት ይሰራሉ?

በኢተርየም ላይ እንደ ማንኛውም ቶከን፣ NFTዎች በዘመናዊ ውሎች ይሰጣሉ። ዘመናዊ ውሉ ምን ተግባራትን እንደሚፈጽም ከሚገልጹት ከበርካታ የNFT መስፈርቶች (በተለምዶ ERC-721 ወይም ERC-1155) ጋር የሚስማማ ነው። ኮንትራቱ NFTዎችን መፍጠር('ሚንት') እንዲሁም ለአንድ ለተወሰነ ባለቤት ሊመድባቸው ይችላል። ባለቤትነት በውሉ ውስጥ የተወሰኑ NFTዎችን ወደ ተወሰኑ አድራሻዎች በማጓደን ይገለጻል። NFT መታወቂያ እና በተለምዶ አብሮት የተያያዘ ሜታዳታ አለው ይህም አንድ የተወሰነን ቶከን ልዩ የሚያደርገው ነው።

አንድ ሰው NFTን ሲፈጥር ወይም ሚንት ሲያደርግ፣ በአድራሻቸው ላይ የተለየ NFTን የሚመድበውን የዘመናዊ ውል ተግባር እየፈጸሙ ነው። ይህ መረጃ የብሎክቼይን አካል በሆነው በውሉ ማከማቻ ውስጥ ይቀመጣል። የውል ፈጣሪው ተጨማሪ አመክንዮ በውሉ ላይ ሊጽፍ ይችላል፣ ለምሳሌ አጠቃላይ አቅርቦቱን መገደብ ወይም ቶከን በተላለፈ ቁጥር ለፈጣሪው የሚከፈለውን ሮያሊቲ መወሰን።

NFTዎች ለምን ይጠቅማሉ?

NFTዎች ለብዙ ነገሮች ይጠቅማሉ ። ከእነዚህም ውስጥ:

  • በአንድ ዝግጅት ላይ መሳተፍዎን ለማረጋገጥ
  • አንድን ስልጠና ማጠናቀቆን ለማረጋገጥ
  • በባለቤትነት ሊወስድዋቸው የሚችሉ የጨዋታዎች እቃዎች
  • የዲጅታል ጥበብ
  • የእውን ዓለም ንብረቶችን በቶክን ለመወከል
  • የኦንላይን ማንነትዎን ለማረጋገጥ
  • ልዩ የሆኑ ይዘቶችን ለማግኘት
  • ትኬት ለመቁረጥ
  • ላልተማከሉ የበይነ መረብ ዶሜይን ስሞች
  • በDeFi ውስጥ ለማስያዣ

ምናልባት NFTዎን በመጠቀም የስራዎችዎን ቁጥጥር ሳያጡ እና ትርፍዎን ለሁለተኛ ወገን መስዋዕት ሳያደርጉ ማጋራት የሚፈልግ አርቲስት ነዎት። አዲስ ውል በመፍጠር የNFTዎችን ብዛት እና ባህሪያቶቻቸውን መወሰን እንዲሁም ክተወሰኑ የስነጥበብ ስራዎች ጋር ማገናኘትን ይችላሉ። አርቲስቱ እንደመሆንዎ መጠን መከፈል ያለብዎትን የሮያሊቲ ክፍያን (ለምሳሌ NFT በተላለፈ ቁጥር 5% የሽያጭ ዋጋ ለውሉ ባለቤት ማስተላለፍን) ወደ ዘመናዊ ውሉ ፕሮግራም ማድረግ ይችላሉ። እንዲሁም ውሉን የለቀቀው ቦርሳ ባለቤት ስለሆኑ NFTዎችን እንደፈጠሩ ሁልጊዜ ማረጋገጥ ይችላሉ። ቦርሳ አድራሻቸው ከዘመናዊ ውሎ ውስጥ ካለ ቶከን ጋር የተቆራኘ ስለሆነ፣ ገዢዎችዎ ከስብስብዎ ትክክለኛ የNFT ባለቤት መሆኖን በቀላሉ ማረጋገጥ ይችላሉ። በእውነተኛነቱ በመተማመን በኢተርየም ሥነ ምህዳር ላይ ሊጠቀሙበት ይችላሉ።

ወይም ለአንድ ስፖርታዊ ዝግጅት ቲኬት ያስቡ። የአንድ ዝግጅት አዘጋጅ ምን ያህል ትኬቶችን እንደሚሸጥ እንደሚመወስን ሁሉ የNFT ፈጣሪዎችም ምን ያህል ቅጂዎች እንዳሉ ሊወስኑ ይችላል። አንዳንድ ጊዜ አንድ አይነት ቅጂዎች ናቸው ለምሳሌ 5000 ጠቅላላ የመግቢያ ትኬቶች። አንዳንድ ጊዜ በርካቶች በጣም ተመሳሳይ ሆነው ነገር ግን እያንዳንዳቸው በትንሹ የሚለያዩ ለየት ባለመልክ ሊመረቱ ይችላሉ ለምሳሌ በቲኬቱ የተመደበ መቀመጫ። ለቲኬት ሻጮች ሳይከፍሉ አቻ ለአቻ ሊገዙ እና ሊሸጡ ይችላሉ እንዲሁም ገዢው ሁልጊዜ የውሉን አድራሻ በማጣራት የቲኬቱን ትክክለኛነት በማረጋገጥ ።

በethereum.org ላይ ሰዎች በእኛ የGitHub ማከማቻ ላይ አስተዋፅዖ እንዳደረጉ ወይም ጥሪዎች ላይ እንደተገኙ ለማሳየት NFTዎች ይጠቅማሉ በተጨማሪም የራሳችን የNFT ዶሜይን ስም አለን። ለethereum.org አስተዋጽዎ ካደረጉ፣ የPOAP NFTን ማግኘት ይችላሉ። አንዳንድ የክሪፕቶ ዝግጅቶች POAPን እንደ ቲኬቶች ይጤቀማሉ። ስለማበርከት ተጨማሪ.

ethereum.org POAP

ይህ ድር ጣቢያ በNFTዎች የተሰራ አማራጭ የዶሜይን ስም አለው ethereum.eth. .org አድራሻችን በዶሜይን ስም ስርዓት (DNS) የቀረበ በማእከላዊነት የሚተዳደረው ሲሆን .eth ደግሞ በኢተርየም ስም አገልግሎት (ENS) በኩል በ ኢተርየም ላይ ተመዝግቧል። እንዲሁም በእኛ ባለቤትነት የተያዘ እና የሚተዳደር ነው። የENS መዝገባችንን ይመልከቱ(opens in a new tab)

ስለ ENS ተጨማሪ መረጃ(opens in a new tab)

የNFT ደህንነት

የኢቴሪየም ደህንነት የሚመጣው ከቀብድ ማረጋገጫ ነው። ስርዓቱ ተንኮል-አዘል ድርጊቶችን በኢኮኖሚ ለማሰናከል የተታለመ ሲሆን ይህም ኢቴሬምን ደህንነቱ የጠበቀ እንዲሆን ያደርገዋል። NFTዎችን እውን የሚያደርገው ይህ ነው። የእርስዎን NFT ግብይት የያዘው ብሎክ አንዴ ከተጠናቀቀ አንድ ሰርጎገን እሱን ለመቀየር በሚሊዮኖች የሚቆጠር ETH ያስከፍላል። ማንኛውም የኢተርየም ሶፍትዌርን የሚያንቀሳቅስ ሰው በNFT ላይ ሐቀኝነት የጎደለው ድርጊት ክተፈጥረ ወዲያውኑ ማወቅ ይችላል፣ እና መጥፎው ተዋናይ በኢኮኖሚ ይቀጣል እና ይባረራል።

የደህንነት ጉዳዮች ከNFTዎች ጋር ተያይዞ ብዙ ጊዜ ከማስመሰል ማጭበርበሮች፣ ከዘመናዊ ውል ድክመቶች ወይም ከተጠቃሚ ስህተቶች (ልክ እንደ ሳያውቁ የግል ቁልፎችን ማጋለጥ) የተገናኙ ስለሆነ፣ ጥሩ የቦርሳ ደህንነትን ለNFT ባለቤቶች ወሳኝ አድርጎታል።

ስለ ደህንነት ተጨማሪ መረጃ

Further reading

Test your Ethereum knowledge

Loading...

ይህ ገፅ አግዞዎት ነበር?